አቀራረብ

አቀራረብ


PANSANTÉ (ፓንሳንቴ) ተደራሽ የሆነ፣ ወጪ ቆጣቢ እንዲሁም ዘላቂነት ያለው የጤና ጥበቃን እጅግ በሚፈለግበት ስፍራ የሚያቀርብ ሲሆን በሚሊዮንየሚቆጠሩ ሰዎችንም ህይወት ያሻሽላል፡፡.

የእኛ የጤና ጥበቃ አቅራቢዎች፣ አርክቴክቶች፣ መሀንዲሶች፣ የአየር ንብረት እንዲሁም የግብዓት ሳይንቲስቶች የአየር ንብረት ለውጥ ጉዳዮችንበአነስተኛ ተጽእኖ እንዲሁም በተቋቋሚነት መፍትሄ የሚሰጥ፤ ይህ በእንዲህ እንዳለም ዘመናዊ የእንክብካቤ ደረጃን አስቸጋሪ የአየር ንብረትሁኔታዎች በሚገኙባቸው እንዲሁም ነባር መሰረተ ልማቶች በሌሉባቸው ስፍራዎች የሚያቀርብ ጽንሰ ሃሳብን አሰናድተዋል::

የምሉእ ዲዛይኑ እያንዳንዱ ገጽታ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እንዲሁም አካባባዊ ዘላቂነትን ግምት ውስጥ ያስገባል፡፡ እና በዲዛይን ዝግጅቱ ላይየአካባቢውን ሰዎች የምናሳትፍ ሲሆን፣ በታዳሽ ሀይል የሚንቀሳቀስም ከኤሌክትሪክ መስመሩ ውቺ የሆነ ምፍትሄንም እናቀርባለን፡፡ የእንቅስቃሴወጪዎችንም ከተለመደው ሆስፒታል ጋር ሲነጻጸር በ50% ያህል እንቀንሳለን፡፡ በዚህ አቀራረብ በቀጥታ አስራ አንዱን የተባበሩት መንግስታት የዘላቂልማት ግቦች እናሳካለን፡፡




የእኛ የዲዛይን ቡድን በጉናር ዴንዊል እና ጄምስ ድራሄም የሚመራ ሲሆን፤ ቡድኑ የሆስፒታል ፕሮጀክቶችን በ3 አህጉራት ውስጥ በሚገኙ 10 ሀገራት ውስጥ እውን የማድረግ ሂደትን ያስተባበረ እና በግንባታዎቹ ላይ የሰራ ነው፡፡ እነዚህ ሆስፒታሎች በድምሩ ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ ዋጋአላቸው፡፡

በአልፕስ ውስጥ ከሚገኘው 500 አልጋዎች ያሉት ሆፒል ጀምሮ በአሜሪካ ውስጥ አስከሚገኘው 1.2 ቢሊዮነድ ዶላር የጦር ተመላሾች የጤና ጥበቃማዕከል ድረስ ያልሰራነው የለም፡፡

የPansanté (ፓንሳንቴ)’s የሆስፒታል ጽንሰሀሳብ የእኛን የተሞክሮ ሀብት በአንድ የተሸሻለ መፍትሄ ላይ አጥልሎ የሚያስቀምጥ ሲሆን፤ ይህምጽንሰሃሳብ የእናንተን የጤና ጥበቃ ፍላጎቶች እንደሚያሟላ እርግጥ ነው፡፡


Share by: