የአካባቢ ምህንድስና

በማስረጃ ላይ የተመረኮዘ ዲዛይን

የአካባቢ ምህንድስና


with Transsolar

ትራንስሶላር የሀይል ፍላጎትን ማሟላት ብቻ ሳሆን ምቾትን፣ ውበትን እንዲሁም ዲዛይን ፍላጎቶችን የሚያሟሉ ፈተራን የተላበሱ መፍትሄዎችንለማቅረብ ይጥራል፡፡ ይህ ልዩ ስፔሻላይዜሽን ማለት እኛ ከበርካታ መሪ የቴክኖሎጂ ልማት ድርጅቶች ጋር አዲስ የቴክኒክ መፍትሄዎችን ለመፈተሽእንዲሁም ለማሻሻል እንሰራለን ማለት ነው፡፡

እነዚህም ከውሃ ስር ፎቶቮላቲክስ ጀምሮ፣ እስከ ንቁ የውሃ ግድግዳዎች፣ ጸጥ ያሉ ማቀዝቀዣዎች እስከ ማይክሮ ሼዲንግ መስኮቶች ድረስ ናቸው፡፡የቴክኒክ መፍትሄዎች ረገድ ዘመናዊ እድሎች መቅረባቸውን እንደምናውቅም እናረጋግጣለን፡፡ በተመሳሳ ጊዜም አነስተኛ ወጪ ንቁ ያልሆኑመፍትሄዎችንም በደንበኞቻችን ፍላጎት መሰረት እናቀርባለን፡፡

የአየር ንብረት ጽንሰሀሳብ ልማት እንዲሁም የዘላቂነት ምህንድስና ማማከር ስራ

ትራንስሶላር አለማቀፍ የአየርንብረት ምህንድስና ተቋም ሲሆን ልዩ፣ በከፍተኛ ደረጃ ምቹነት ያለው የቤት ውስጥ እንደሁም የውጪ ስፍራንበአዎንታዊ የአካባቢ ተጽእኖ ለመፍጠርም አላማው አድርጎ እየሰራ ይገኛል፡፡ ግሩም ስነህንጻ ለመፍጠር የተወሰዱት እርምጃዎች የግብዓትአጠቃቀምን ይቀንሳሉ ብለን እናምናለን፡፡ ለእኛ፣ ዘላቂነት ከዲዛይን የተለየ ይደለም፡፡ ይልቁንም የተገነባውን አካባቢ ተሞክሮ የሚያሳድግ እጅግየማይናቅ ወሳኝ አካል ነው፡፡



rበ1992እ.ኤ.አ ከተመሰረተ በኋላ፣ ትራንስሶላር በፍጥነት የተጠናቀረ ለአየርንብረት ምላሽ የሚሰጥ ዲዛይንን ጽንሰሀሳብ በጀርመን ውስጥበማስተዋወቅ በፍጥነት ታውቋል፣ እየጨመረ የሚሄድ ህብረትንም በአለማችን ከፍተኛ ደረጃ የሚገኙ አርክቴክቶች ዘንድ በማምጣትም ታዋቂሊሆን ችሏል፡፡ በሰሜን አሜሪካ ውስጥ የእና የትብብር ዘዴ ለበርካታ ፕሮጀክቶቻችን የተለያዩ የAIA ክብሮችን እንዲሁም የCOTE  ምርጥ አስርስጦታዎችን ስገኙ ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ የደረስንበት ከፍተኛ ነጥብም በ 2015 AIA ተቋም የትብብር ስኬት ክብርን መቀዳጀታችን ነበር፡፡ ዛሬ፣ የእኛወደ 50 የሚጠጉ መሀንዲሱች በስቱትጋርት፣ ሙኒክ፣ ኒው ዮርክ እንዲሁም በፓሪስ የሚገኙ ጽ/ቤቶች ውስጥ ተበታትነው የሚገኙ ሲሆን በ122 ሀገራት ውስጥም ከ2000 በላይ ለሚሆኑ ፕጀክቶች አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡s.


የተገነባው አካባቢ ከአካላዊ ህንጻው በላይ መሆኑን እናምናለን፡፡ የእኛ አቀራረብ በነዋሪዎች ተሞክሮ ላይ ተጽእኖ የሚኖራቸውን ሁሉንም ሁኔዎችይዳስሳል፡፡ በውስጥም ሆነ በውቺ  አየርንብረት ሁልጊዜም ይቀያየራል፡፡ እኛ ልዩ የሆኑ መፍትሄዎችን በመስጠት በእንደዚህ አይነት ተፈጥሯዊተለዋዋጭነትላይ መፍትሄዎችን እናቀርባለን፡፡ የእኛ የመገልገያ አይነቶች ሁልጊዜም በሲሙሌሽን ሞዴሎች ፣ በልዩ ሶፍትዌሮች አማካኝነት እያደጉየሚገኙ ሲሆን፣ በተፈላጊ መልኩ የተዘጋጀ የምህንድስና ትንተናን፣ አካላዊ ምርምሮችን በመጠቀምም፣ ቴክኖሎጂ ለብቻው መልስ እንዳልሆነእንረዳለን፡፡ ንቁ ያልሆነ የዲዛይን ስልትን በመተግበር ረገድ እኛ ፈር ቀዳጆች ነን፡፡ በተጨማሪም አነስተኛ እና ትልቅ ተገነቡ ትልልቅ ፕሮጀክቶች ላይየሚገኙ አተገባበሮች ላይ  ኩራት ይሰማናል፡፡


የእኛ ውጤት ሂደት ነው፡፡ እኛ ከባድ ጥያቄዎችን እንጠይቃለን፡፡ የተለመደውን አሰራር በመገዳደርም አዲስ መፍትሄዎችን እናቀርባለን፡፡በተጨማሪም ሀሳቦችን በጥልቀት እንመረምራለን፡፡ እያንዳንዱ ፕሮጀክት እውቀት መጋራትን እንዲሁም አዲስ ሀሳቦችን መፍጠርን ይፈልጋል፡፡በመጨረሻም ልዩ ተሞክሮዎችን መፍጠር ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ተመሳሳይ ግብን እውን በማድረግ ላይ እንሰራለን፡፡ ከፍተኛ ምቾትንየምናስጠብቅ ሲሆን፣ አነስተኛ ተጽእኖም ይኖራል፡፡

Share by: