ለወደፊት የጤና ቀውሶች ይበልጥ መዘጋጀታችንን እንዴት ልናረጋግጥ እንችላለን?
የህዝብ ቁጥር መጨመር እና የከተማ መስፋፋት በጤና አጠባበቅ መሠረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ጫና ይፈጥራሉ። የወጪ መጨመር፣ የተገደበ በጀት እና የፋይናንስ አቅርቦት ውስንነት በቂ የጤና አገልግሎትን ለብዙ የህብረተሰብ ክፍሎች ማድረስ የበለጠ ከባድ ያደርገዋል።
በመስከረም 25/2015 (እ.አ.አ) ሁሉም የተባበሩት መንግስታት አባል ሀገራት ድህነትን ለማጥፋት፣ ፕላኔቷን ለመጠበቅ እና ለሁሉም ብልጽግናን ማረጋገጥ እንደ አዲስ የዘላቂ ልማት አጀንዳ ግቦች በማድረግ አውጥተዋል። እያንዳንዱ ግብ በሚቀጥሉት 15 ዓመታት ውስጥ ሊደረስባቸው የሚገቡ የተወሰኑ ግቦች አሉት፡፡
ፓንሰንቴ ይህንን ራዕይ ይደግፋል እንዲሁም በምናከናዉነዉ በዘላቂ ሆስፒታል ልማት በቀጥታ በተጠቀሱት የተባበሩትመንግስታት ዘላቂ ልማት ግቦች ስኬት የጎላ ሚና እንጫወታለን፡፡ .
"በ PANSANTÉ (ፓንሳንቴ), በክፍልፋዮች (ሞዱሎች) ላይ የተመሰረተ የሆስፒታል ጽንሰሀሳብ ያዘጋጀን ሲሆን፤ ይህም ሙሉ በሙሉ ብቁ የሆኑ፣የመስክ አየርንብረት ለውጥ ሙሉ ምህዳርን ተከትሎው የሚሰሩ፣ ነባር መሰረተ ልማትን ያገናዘቡ እንዲሁም የእያንዳንዱን የማህበረሰብ አባልፍላጎቶች ያገናዘቡ በርካታ ሙሉ አቅም ያላቸው ሆስፒሎችን ለመገንባት ያስችለናል፡፡ እኛ መፍትሄ ለረጅም ጊዜ ወጪ ቆጣቢ ሆነው የሚቆዩሆስፒሎችን በአብዛኛው የአለማችን ክፍል ውስጥ ለመገንባት ያለውን ሰፊ ፍላጎት ነባራዊ የአየርንብረት ቀውስ ለንግድ እና ግንባታ አዲስአቀራረብ የሚፈልግ ከመሆኑ ጋር በተጣጣመ መልኩ የሚያመዛዝን ነው፡፡."
Gunnar Dennewill ስራ አስፈጻሚ ቦርድ
PANSANTÉ
ምሉዕ በሆነ መፍትሄ እያደገ ለሚገኘው የጤና ጥበቃ ፍላጎት ምላሽ መስጠት!